ኣሪቲ (Artemisia afra) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
በጣም የሚሸተት ቊጥቋጣም ዕጽ ነው።
አንዳንዴ «ጭቁኝ» ቢባልም ያው በውነት የተዛመደ ዝርያ A. abyssinica ነው።
በሚያብባው ጊዜ ይመረታል።
በደጋ ይገኛል፣ በእርጥብ ጉድጓድና በሜዳ ምንጊዜም ይገኛል።
አሪቲ የሆድ ቁርጠት ለማስታገሥ ይጠቀማል። የተደቀቁ ቅጠሎች ከውኃ ወይም ከማር ጋራ ተቀላቅለው በአፍ ይሰጣል።
አስደሳች መዓዛ ስላለው እቃ ለማጽዳት ይጠቀማል።[1]
የA. afra ቅጠል እና ነጭ ሽንኩርት ለወባ መጠቀሙ በፍቼ ወረዳ ተዘገበ።[2]