dcsimg

እንኮይ ( Amharic )

provided by wikipedia emerging languages
Ximenia americana leaves & fruit at Chilkur near Hyderabad, AP W2 IMG 7288.jpg

እንኮይ (Ximenia americana L.) በኢትዮጵያ የሚበቅል እጅግ ጣፋጭ የሆነ ቢጫ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው።

የእንኮይ ተጨማሪ ጥቅም

ፍራፍሬውን በብዛት መብላት ትልን ይገድላል።

የእንኮይ ዘር ግን መርዛም ነው።[1]

በአንድ ናይጄሪያ ዩኒቨርሲቲ ምርመራ፣ የተለያዩ ተውሳኮችን እንደሚገድል ተረጋገጠ።[2]ፍሎሪዳ ክፍላገር አሜሪካ ጥንታዊ ኗሪዎች ልጡ በጡንቻ ወይም ድድ ሕመም ላይ ማከሙን ያውቁ ነበር።[3]

ቅጠሉ ትንሽ መርዝ አለውና ሳይበላ በደንብ መበሰል ያስፈልጋል። ቅጠሉ ጉሮሮ ሲደርቅ፣ ለአሜባ፣ ለውሻ በሽታ ያገለግላል።

እንኮይ ተስማሚ የሆነ አየር ጠባይና መሬት

ከ2000 ሜትር በታች እስከ 7 m. ይደርሳል። በቆላና በገሞጂ አገራት ይገኛል።

የእንኮይ አስተዳደግና እንክብካቤ

ቅጠለ ረገፍ ዛፍ ወይም ቊጥቋጥ ነው። ቅጠሉ እንደ ለውዝ (አልመንድ) ይሸታል።

  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ Short Communication: Studies of antimicrobial activity and chemical constituents of Ximenia americana. DS Ogunleye and SF Ibitoye, Trop J Pharm Res, December 2003, 2(2), pages 239-241 (abstract)
  3. ^ 50 Common Native Plants Important In Florida's Ethnobotanical History by Ginger M. Allen, Michael D. Bond, and Martin B. Main. University of Florida IFAS Extension. http://edis.ifas.ufl.edu/uw152
license
cc-by-sa-3.0
copyright
ዊኪፔዲያ ደራሲያን እና አርታኢዎች