dcsimg

ጫት ( Amharic )

provided by wikipedia emerging languages
 src=
ጫት

ጫት ወይንም በርጫ፡ በርጫ በምስራቅ አፍሪካና በየመን የተለመደ ቅጠል ነው። የጫትን ቅጠል በማኘክ 'ምርቃና' የሚባል ቃሚዎቹ ተወዳጅ ስሜት ነው የሚሉት ላይ መድረስ ይቻላል። ይህ የሚሆነው ጫት ውስጥ ያሉት ንጥረ ነግሮች ኣንጎል ላይ በሚፈጥሩት ለውጥ ሲሆን የጫት ወይም ጅማ የስነ ፍጥረት ስሙ በእንግሊዝኛ Catha edulis ነው። ጫት የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ይባላል።

የጫት ዝርያዎች በኤትዮጵያ ወስጥ በተለያዪ ክፍለ ሃገራት ይገኛል። እንደየአገሩም የጫት (የተክሉ) ዓይነት እና በወስጡ ያለው ንጥረ ነገር ጥንካሬ (የምርቃና ሃይል) ይለያያል። በሃረር እና በአካባቢው የሚገኝ የጫት ዓይነት (ዓወዳይ) የሚባል ሲሆን ቅርንጫፎቹ ረጃጅም ቅጠሉ ደግሞ ሰፋ ያለ (ከሌሎች የጫት ዓይነቶች ጋር ሲተያይ) በወንዶ ገነት አካባቢ የሚገኘው ደግሞ 'ወንዶ ገነት' የሚባል ሲሆን የማስከር (የምርቃና) ሃይሉ ከዓወዳይ እንደሚበልጥ ይነገራል። የተክሉ ዓይነት፡ ቅርንጫፎቹ ቀጫጭን እና አጫጭር፣ ቅጠሉም ቀጠን ብሎ ዓወዳይን ያህል ወዝ የሌለው። ጫት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልላት በተለያየ አይነት መልኩ በመቃም ላይ ይገኛል። ለአብነትም በአማራ ክልል ውስጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ የጫት አቃቃምም ሆነ አሰፋፈሩ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በፍፁም ይለያል ይኅውም በሌላው የሀገራችን ክፍል ጫት ከነ ገረባው ወይም እንጨቱ በአነስተኛ ፕላስቲክ ተደርጎ ሲሸጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ ግን የጫቱ ቅጠል ሊቃም ከሚችል የጫቱ ለስላሳ የግንድ ክፍል ጋር ተቀንጥሶ በሚዛን ከ25 ግራም ጀምሮ እስከ ብዙ ኪሎዎች ይሸጣል። ብዙ ጊዜ ጫት መቃም ከጥቅሙ ጉዳቱ ቢብስም አንዳንድ ጥናቶች ግን ጫት ልክ እንደመድሀኒትም ያገለግላል ይላሉ። ጫት አትኩሮትን ሙሉ በሙሉ ሰርቆ ትውስታን በመንጠቅ ህይወትን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚከታት Attention Deflict Disorder ከተባለው በሽታ ነፃ እንደሚያወጣ ይነገራል።

ዩናይትድ እስቴትስ በጫት መጠቀም ክልክል ነው።

ተክሉ

ዛፉ እስክ 7 ሜትር ወይም አንዳንዴ 15-20 ሜትር ይቆማል።

የአረብኛው ስሙ /ጛአት/ ሲሆን የዚህም በፊደል ቁጥር ድምር 501 ሲሆን፣ ጫት 501 ልዩ ልዩ እርጉሞች እንዳሉበት በአንዳንድ አጓጉል እምነት ተገኝቷል።

ሥሩ በአንዳንድ ቦታ ለግሪፕ (ኢንፍሉዌንዛ)፣ ለሆድ ወይም ደረት ችግሮች ተጠቅሟል።

የቅጠሉ አደንዛዥ ውጤት ከድካም ወይም ከረሃብ ያስታግሣል።

ጫትና ጌሾ በእኩል መጠኖች ጥራት ያለ ጠጅ ይሠራል። ይህ ጥራት ከ፰ ቀን በኋላ ግን ይጠፋል።[1]

የጫት ቅጠልና የእንጭብር ሥር ተድቅቀው በቅቤ ለአስማ መሳል ይጠጣል።[2]

የውጭ መያያዣዎች

  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
license
cc-by-sa-3.0
copyright
ዊኪፔዲያ ደራሲያን እና አርታኢዎች

ጫት: Brief Summary ( Amharic )

provided by wikipedia emerging languages
 src= ጫት