dcsimg

ዓሣ ( Amharic )

provided by wikipedia emerging languages
541px-Georgia Aquarium - Giant Grouper edit.jpg

አሳ ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር ባለጥንድ ስንጥብ እና ብዙ ነጠላ ስንጥቦች የጀርባ አጥንት ያለው እንስሳ ነው። አብዛሀኛዎቹ የአሳ ዝርያዎች ደመ ቀዝቃዛ ሲሆኑ እንደ ውሀው መጠነ ሙቀት የራሳቸውን ሰውነት አስማምተው መኖር ይችላሉ።

የዓሣ ዝርያዎች

 src=
አሳ ተራ በአዋሳ

ትልቅ-አፍ ባስ

 src=
ትልቅ-አፍ ባስ

ትልቅ-አፍ ባስ የሚባለው የለጋ ውሃ የዓሣ ዝርያ ሲሆን፡ በአማካኝ እስከ 11ኪሎ ድረስ ይደርሳል። ባስ የሠንፊሽ፡ ማለትም የፀሃይ ጨረር መሳይ ስንጥብ ያላቸው አሳዎች ቤተሰብ ነው።

ቀስተደመና ትራውት

ቀስተደመና ትራውት

ሙሉ ለሙሉ ያደገ የጅረት ቀስተደመና ትራውት ዓሣ ከ0.5 እስከ 2.3ኪሎ ሲመዝን፤ በሀይቅ ውስጥ የሚኖር ቀስተደመና ትራውት ደግሞ እስከ 9.1ኪሎ ድረስ ይመዝናል።

ካትፊሽ

ካትፊሽ (አምባዛ)

ሳመን

 src=
ሳመን ዓሣ ቢቨር ግድብን ዘሎ ሲሄድ

ሳመን በለጋ ውሃ ተወልደው ወደ ውቅያኖስ ከሚፈልሱት የዓሣ ዝርያዎች አንዱ ነው። ሆኖም በርካታ የሳመን መንጋዎች እድሜያቸውን ሙሉ በለጋ ውሃ ለማሳለፍ የተወሰኑ በመሆናቸው የለጋ ውሃ አኗኗር ዘዴዎችን መርጠው እንደሚኖሩ ይታወቃል። የሳመን እንቁላል፡

ናይል ፐርች

ያደገ ናይል ፐርች በአማካኝ እስከ 121–137ሴ.ሜ. የሚደርስ የዓሣ ዝርያ ሲሆን፡ በጣም ትልቅ የሚባለው እስከ 200ኪሎ ድረስ ይመዝናል።

ብሉጊል

ብሉጊል የሠንፊሽ ቤተሰብ የለጋ ውሃ ዓሣ ነው። ብሉጊል፡ ወይንም ሰማያዊ-ስንጥብ የሚባለው የስንጥቦቹ ማለቂያ ደማቅ ሰማያዊ ስለሆነ ነው።

የለጋ ውሃ ሎብስተር

የለጋ ውሃ ሎብስተር (ጐርምጥ)፣ ክሮውፊሽ፣ ወይንም ደግሞ ክሬይፊሽ ተብሎ የሚታወቀው እስከ 17.5ሴ.ሜ ድረስ ይረዝማል።

ተላፒያ

 src=
ተላፒያ

ተላፒያ ወደመቶ የሚሆኑ የተለያዩ ዓሣዎች ቤተሰብ የጋራ መጠርያ ነው። ተላፒያ በጠቅላላው ከ21 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የማያንስ ሙቀት ያለው ለጋ ውሃ ውስጥ የሚኖሩ ዓሣዎች ናቸው።

ሸርጣን

ዋና መጣጥፍ፦ ሠርጣን

 src=
ሸርጣን

ክራፒ

 src=
ጥቁር ክራፒ

ክራፒ፡ ወይንም ሳክ-ኦ-ሌ፡ የሠንፊሽ ቤተሰብ ሲሆን፡ ከለጋ ውሃ ዓሣዎች በጣፋጭነቱ ይታወቃል።

ኮድ

ሮክፊሽ

 src=
ስትራይፕድ ባስ

ስትራይፕድ ባስ በአማካኝ ከ67 እስከ100ሴ.ሜ. ረዝሞ ከ4.5 እስከ14.5 ድረስ የሚመዝን የሮክፊሽ አይነት ነው። ስትራይፕድ ባስ ሥጋ ነጭ ቀለም፣ ልዝብ ጣዕምና መካከለኛ ገጽታ አለው፤ እጅግ በጣም ሁለገብ በመሆኑም በተለያየ አይነት መልክ ማብሰል ይቻላል፦ በመጥበሻ መለብለብ፣ በግሪል መጥበስ፣ በእንፋሎት ማብሰል፣ በኮርቡዮን ፖች ማድረግ፣ አሮስቶ፣ በኦቨን ብሮይልድ፣ ሳውቴ የተደረገ፣ ፍራይድ ወይንም ደግሞ ባተር ተደርጎ ፍራይድ። የስትራይፕድ ባስ ሥጋ ጥሬ ወይንም ደግሞ ፒክል አድርጎም መመገብ ይቻላል።

ማከረል

 src=
ማከረል

ማከረል የኦሜጋ-3 ዘይት ይዘቱ ከፍተኛ ስለሆነ፡ በዓሣ አጥማጆች በጣም የሚፈለግ የዓሣ ዝርያ ነው። ማከረል በማንኛውም ውቅያኖስ የሚገኝ ሲሆን፡ በ2009እ.ኤ.አ፡ ከአምስት ሚሊዮን ቶን በላይ ማከረል ዓሣ ተጠምዿል።

ስናፐር

የአውሮፓ ባስ

የአውሮፓ ባስ የውቅያኖስ ዓሣ ሲሆን፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በለጋ ውሃ ውስጥ ይገኛል።

ሽርምፕ

 src=
ሽርምፕ

በአለም ላይ ካለው ሽርምፕ (ሸርጥ አሣ) ወደሩብ የሚሆነው በለጋ ውሃ ይገኛል።


ኢትዮጵያ - የአፍሪካ የውኃ ማማ እና ዓሣዎቿ

license
cc-by-sa-3.0
copyright
ዊኪፔዲያ ደራሲያን እና አርታኢዎች